05 Aug2023
ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ሁሉም መደበኛ የቅድመና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች ከዛሬ ሓምሌ 29/2015ዓ/ም ጀምሮ እየተቀበለ ይገኛል።
በትግራይ በነበረው ጦርነት ምክንያት ለሁለት ዓመት የመማር ማስተማር ስራው ኣቋርጦ የነበረው ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ መሰረታዊ የሚባል ጥገናዎች በማድረግ ሁሉም መደበኛና የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ከዛሬ ሓምሌ 29 እስከ ነሓሰ 01/2015 ዓ/ም እየተቀበለ ይገኛል ።
ማክሰኞ ነሓሰ 02/2015 ዓ/ም የዩኒቨርስቲው ቦርድ ኣባላት፣የዩኒቨርስቲው ማሕበረሰብ፣የከተማው የሃይማኖት መሪዎች ፣ የሃገር ሽማግሌዎች ፣ የንግድ ማሕበረሰብ ተወካዮችና እንዲሁም የከተማና የዞን ኣመራሮች በሚገኙበት ደማቅ የኣቀባበል ፕሮግራም ይዘጋጃል ።
ውድ የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንኳን ወደ ዩኒቨርስቲያችሁ በሰላም መጣችሁ ።