የተማሪዎች ጥሪ ማስታወቅያ
በ2018 ዓ/ም በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለተመደባቹ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ
ዓድግራት ዩኒቨርስቲ በ2018ዓ.ም የተመደቡ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎችን የሚቀበልበት የመግብያ ቀን ታሕሳስ 06 እና 07, 2018ዓ.ም በመሆኑ በተጠቀሰዉ ቀናት ብቻ በዩኒቨርሲቲዉ ሬጅስትራር ፅ/ቤት በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እየገለፅን ትምህርት የሚጀመረዉ ታሕሳስ 08, 2018ዓ.ም መሆኑን እናሳዉቃለን።
ማሳሰብያ
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ
የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው
ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
መጠኑ 3×4 የሆነ የቅርብ ጊዜ አራት ፎቶግራፍ
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)
ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda)
ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ
ከተጠቀሱት ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ ለሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲዉ የማያስተናግድ መሆኑን እናሳዉቃለን