የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ በዩኒቨርስቲው ለሚገኙ ሴት ኣመራሮች የኣቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠናው መድረክ ተገኝተው ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ኣካቶ ትግበራ ስራ ኣስፈፃሚ ወ/ሮ ይርጋለም ነጋሽ ስልጠናው ሴቶች በአመራርነት ላይ ያላቸውን ችሎታ እንድያዳብሩና ተነሳሽነት እንድያሳዩ በማድረግ ወደ አመራርነት እንዲመጡ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ አንደሆነ ተናግረዋል። ወ/ሮ ይርጋለም በማከልም ይህን ስልጠና ወስደው ከመምራት ባለፈ ሌሎችንም በማብቃት ወደ አመራርነት ማምጣት መቻልና እንደ ዩኒቨርሲቲም የአሰራር ስርአታችንን በመፈተሽ ብቁ የሆኑ ሴቶችን ወደ አመራርነት ለማምጣት ስልጠናውን በትኩረት መውሰድና ራስን ማብቃት ይጠበቅብናል ሲሉ መልእክታቸውን ኣስተላልፈዋል።
ሰልጣኞቹ ከስልጠናው በርካታ ልምዶችና ተሞክሮዎችን እንዳገኙበት፤ እርስ በእርስ እንዲማማሩና እንዲተዋወቁም ጭምር እንዳደረጋቸውና የዚህ አይነት ስልጠናዎች ቀጣይነት ቢኖራቸው እነሱም በስራቸው ላሉ ባለሙያዎች አርዓያ መሆን የሚችሉበት ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡
ስልጠናው በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የማኔጅመንት መ/ር ወንድሙ ሓለፎም ተሰጥቷል።
በመጨረሻም ሰልጣኞቹ ዩኒቨርስቲ ለህፃናት ማቆያ (Day care) የሚሆን ህንፃ የስራው ሂደት ያለበትን ደረጃ ጎብኝቷል።