11 May2023
የቅድመ ምዝገባ መረጃ
1. የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች ሆናችሁ ላላፉት ሁለት ዓመታት በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድባችሁ የመማር እድል ያላጋጠማችሁ፤
2. በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተከታታይ መርሃ ግብር ተማሪዎች፤
3. በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በመደበኛነት ስትማሩ ቆይታችሁ፣ ላለፉት ሁለት አመታት አቛርጣችሁ አሁን ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለመመዝገብ የምትፈልጉ ለመረጃ ያህል ስለሚፈለግ፣
በዩኒቨርሲቲው http://sims.adu.edu.et/ በኦንላይን የቅድመ ምዝገባ ቅፅ ከግንቦት 03 አስከ 15/2015 እንድትሞሉ እናሳውቃለን። ትምህርት የሚጀመርበት ቀን ደግሞ በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል።