04 Dec2017
ዓዲ-ግራት ዩኒቨርስቲ ለዘጠኝ ወረዳዎች የመፅሓፍ ልገሳ ኣደረገ
ዓዲ-ግራት ዩኒቨርስቲ ከ 1.3 ሚልዮን በላይ ብር በማውጣት ወደ 10,000 (ኣስር ሺ) የሚጠጉ መፃሕፍቶች በምስራቃዊ ዞን የሚገኙ 9(ዘጠኝ) ወረዳዎች በእገዛ መልክ ኣስረክብዋል። በርክክቡ ግዜ የተገኙ የዞኑ ም/ኣሰተዳድር ኣቶ ወ/ኣብርሃ ገ/ፃድቅ ዩኒቨርስቲው በእድሜው ትንሽ ቢሆንም በማህበራዊ ኣገልግሎት ዘርፍ እየሰራው ያለው ስራ በማድነቀ እገዛው ቀጣይነት እንዲኖረው ጠይቅዋል። የዩኒቨርስቲው ፕረዚደንት ዶ/ር ዛይድ ነጋሽም ዩኒቨርስቲው ትምርት ጥራት በኣከባቢው ባሉ ትምህርት ቤቶች እንዲረጋገጥ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የተለያዩ ስራዎች እየሰራ እንዳለና ድጋፉም ኣጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል ገብትዋል።