16 Dec2016
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2009 ዓ/ም
ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የ2009 ዓ/ም በጀት ዓመት የትምህርት ዘመን ሶስተኛ ግልፅ ጨረታ ለተማሪዎች ኣገልግሎት የሚውል የምግብ ግብኣት ኣቅርቦት፣ የስፖርት ዕቃዎች ፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የክችን ዕቃዎች፣ የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ደንብ ልብስ ኣቅርቦት፣ የደረቅ ዕንጨት ኣቅርቦት፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና የፅዳት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ Download Detail Specification for each Lot:
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለውና ፍቃዱንም በዘመኑ የታደሰ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- በቀረበው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችል
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቹ TIN ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችል
- ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ
- ብር 100,000.00 በሎት 1 ስር ለሚገኝ የዳቦ አቅርቦት እንዲሁም ሌሎች በሎት 1 ስር ለሚገኙ አቅርበቶች ብር 30,000.00 ሲሆን
- ለተቀሩት ሎቶች ለያንዳንዳቸዉ ብር 50,000.00 በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ስም ማስያዝ የሚችል፡፡
- ለተማሪዎች ኣገልግሎት የሚውል የምግብ ግብኣት ኣቅርቦት (ሎት 1)
- የስፖርት ዕቃዎች (ሎት 2)
- የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች (ሎት 3)
- የክችን ዕቃዎች ( ሎት 4)
- የፈርኒቸር ዕቃዎች ( ሎት 5)
- የደንብ ልብስ ኣቅርቦት ( ሎት 6)
- የደረቅ ዕንጨት ኣቅርቦት ( ሎት 7) (ለሁለተኛ ግዜ የወጣ)
- የኤሌክትሪክ ዕቃዎች (ሎት 8)
- የፅዳት ዕቃዎች (ሎት 9)
- ተጫራቾች የማቅረቢያ /የአቅራቢ/ ሰርተፊኬት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው
- ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ከዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት ኣስተዳደር ዳይሬክቶሬት ፅ/ቤት ህንፃ/ብሎክ/ ቁጥር 13 ክፍል 07 መውሰድ የሚችል ሲሆን ዋጋው መቅረብ ያለበት ደግሞ ከዩኒቨርሲቲው በሚሸጥ ኦርጅናል ዶክመንት ብቻ መሆን ኣለበት ።
- ማንኛዉም ተጫራች ከዩኒቨርሲቲዉ የገዛዉ የጨረታ ሰነድ ዶክሜንት ፈርሞና ማህተም ኣድርጎ ምንም ሳያጓድል በተዘጋጀለት የጨረታ ሰነድ ማስገባት ኣለበት ።
- የጨረታ ሰነድ ማስታወቅያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 5:30 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ከሰአት ልክ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀን ተብሎ የተጠቀሰዉ 16ኛዉ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ሃገራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
- ዝርዝር ስፔስፊኬሽን በድህረ ገፅ http://www.adu.edu.et ወይም http://www.ppa.gov.et ማግኘት ይቻላል፡፡
- ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ ማብራሪያ ፡- ስ.ቁ 0344452318 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡