02 Aug2023
የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ከፍተኛና መካከለኛ ኣመራሮች በዩኒቨርስቲው የተለያዩ ክፍሎች ጎበኙ
ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከሓምሌ 29 እስከ ነሓሰ 01/2015 ዓ/ም መደበኛ ተማሪዎቹን ይቀበላል። በዚህም መሰረት የዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት፣ም/ፕረዚዳንቶች፣ ዲኖችና ዳይሬክተሮች ዩኒቨርስቲው ተማሪ ለመቀበል በተለያዩ ክፍሎች ያለው ዝግጅት በኣካል ተመልክቷል። በጉብኝቱ ለማረጋገጥ እንደተቻለው ዩኒቨርስቲው ተማሪዎቹ ለመቀበል እየሰራው ያለው ስራ የሚደነቅ ሲሆን መስተካከል የሚገባቸው ነገሮች ላይም በስራ ሓላፊዎች የተለያዩ ሃሳቦች ቀርበዋል።