07 Apr2023
የትምህርት ምኒስቴር ከፍተኛ ኣመራሮች በትግራይ ያለው የመማር ማስተማር ሂደት ለመገምገም መቀለ ተገኝተዋል::
የትምህርት ምኒስቴር ድኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ እንዲሁም ከፍተኛ ኣመራር የሆኑት ዶ/ር ሰለሙን ኣብርሃን ጨምሮ የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝደንትና የከፍተኛ ትምህርት ተቃማት ኮንሰርቴም ሰብሳቢ ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና የባህርዳር ጅማ ደብረብርሃንና ሰመራ ዩኒቨርስቲዎች ፕረዚደንቶች በትግራይ ያሉ ዩኒቨርስቲዎችና ኣጠቃላይ ትምህርት ያለበትን ቁመና ለመገምገም መቀለ ተገኝተዋል:: በፕላኔት ሆቴል በተደረገው ስብሰባ በትግራይ የሚገኙ የኣራቱም ዩኒቨርስቲ ፕረዚደንቶች ዩኒቨርስቲዎች ያሉበት ደረጃ የሚያሳይ ሪፓርት ኣቅርበዋል::
በተጨማሪም የትግራይ ኣጠቃላይ ትምህርት ያለበትን ደረጃ በክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ ቀርበዋል:: ኣመራሮቹ ሪፓርቱን ካቀረቡ ብሃላ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በተለይ ዩኒቨርስቲዎች ባለው ኣቅም ስራ ጀምረው የወደመው በሂደት እንዲተካ እንዲያደርጉ የትምህርት ምኒስቴር ድኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ኣሳስበዋል:: የኢትዮጵይ ከፍተኛ ትምህርት ተቃማት ኮንሰርቴም ወክለው የመጡ ኣመራሮች ኮንሰርቴሙ በቀጣይ በትግራይ ላሉ ዩኒቨርስቲዎች ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል በመግባት ለግዜው በኮንሰርቴሙ ስም የ20 ሚልዮን ድጋፍ ኣድርገዋል::
በውይይቱ የትግራይ ማህበራዊ ጉዳይ ክላስተር ኣስተባባሪ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት የተሳተፉ ሲሆን በውይይቱ ማጠቃልያ የትግራይ ግዝያዊ መስተዳድር ፕረዚደንት ኣቶ ጌታቸው ረዳ ተገኝተው ዋና ትኩረታችን ከትምህርት ርቆ የነበረው ትውልድ ወደ ትምህርት እንዲመለስ ማድረግ ነው ብለው በኣፅንኦት ተናግረዋል:: ዩኒቨርስቲዎች ላደረጉት ድጋፍም ምስጋናቸው ኣቅርበዋል::




