25 Jul2023
ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ የመማር ማስተማር ሂደት ዳግም ለማስጀመር የዩኒቨርስቲው ካውንስል ውይይት ኣካሂዷል።
ዩኒቨርስቲው ለሁለት ዓመት ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ሂደት ለማስጀመር የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች ስያካሂድ ቆይቷል። በዩኒቨርስቲ ደረጃ ሲካሄዱ የነበሩ የዝግጅት ስራዎች ተማሪዎች ለመቀበል ዩኒቨርስቲው ያለበት ደረጃ የሚገመግም ከትምህርት ክፍል ሓላፊ ጀምሮ የሚገኙ ኣመራሮች የተሳተፉበት ውጤታማ የምክክር መድረክ ተካሂዳል ። በመድረኩ ሁሉም ኮሌጅ ዲኖች፣ ሬጅስትራር ፣ የፍሬሽማን ፕሮግራም ኣስተባባሪና የተማሪዎች ዲን በየስራ ክፍሎቻቸው ያለው ዝግጅትና ያሉቧቸው ፈተናዎች በዝርዝር ኣቅርበው ውይይት ተካሂዶበታል።
የመድረኩ ተሳታፊዎችም ዩኒቨርስቲው ደርሶበት ከነበረው መጠነ ሰፊ ውድመት በፍጥነት ለመነሳት የሚደግፉ ሓሳቦች አጋርተዋል። በመጨረሻም የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ ኣመራሮች ከመድረኩ በተነሱ ሓሳቦችና ኣጠቃላይ የዝግጅት ስራ በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥቷል።