08 Aug2023
ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ለሁሉም ነባር ተማሪዎቹ እና ለ12 ክፍል ተማሪዎች ደማቅ የኣቀባበል ፕሮግራም ኣካሂዷል።
እንደሚታወቀው በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ዩኒቨርስቲው ከፍተኛ ውድመት ደርሶበት ለሁለት ዓመት የመማር ማስተማር ስራው ኣቋርጦ ቆይቷል። ከሰላም ስምምነቱ ብኋላ ዩኒቨርስቲው መሰረታዊ የሚባሉ የጥገና ስራዎች በመስራት ሁሉም የቅድመና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች ተቀብሏል።
በዛሬ ዕለት ነሓሴ 02/2015 ዓ/ም ለተማሪዎቹ ደማቅ የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕርግራም ተዘጋጅቷል። በፕሮግራሙ በትግራይ ግዝያዊ መስተዳድር የማሕበራዊ ዘርፍ ሓላፊ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት፣ የትምህርት ቢሮ ሓላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ፣ የምስራቃዊ ዞን ኣስተዳዳሪ ኣቶ ሽሻይ መረሳ፣ የዓዲግራት ከተማ ከንቲባ ኣቶ ሰለሙን ሓጎስ፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ተገኝተዋል። ዶ/ር ዛይድ ነጋሽ፣ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት፣ ኣቶ ሰለሙን ሓጎስ፣ የሃይማኖት መሪዎች እና የተማሪዎች ሕብረት ተወካይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ኣስተላልፈዋል።
ዶ/ር ዛይድ ነጋሽ የዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት በመልእክታቸው ዩኒቨርስቲው ከደረሰው ውድመት ኣንፃር ወደነበረበት ለመመለስ ብዙ በጀትና ጥረት ስለሚፈልግ የመማር ማስተማር ስራ ለማስጀመር የሚያስፈልግ መሰረታዊ የጥገና ስራ ተሰርቷል ብሏል። ፕረዚዳንቱ ኣክለው እስከ ዛሬ ወደዩኒቨርስቲው ሪፓርተር ያደረጉ 2091 መደበኛ 1983 የ12 ክፍል ጠቅላላ 4126 ተማሪዎች ናቸው።
