በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተቀናጀ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ስርአት መሰረት ያደረገ ኦሬንቴሽን ተሰጠ፡፡

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለሚመለከታቸው ዲኖች፣ ትምህርት ክፍል ሓላፊዎች፣ አስተዳደር ዘርፍ ሀላፊዎችና ሰራተኞች የተቀናጀ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ስርአት የወረቀት ስራን ወደ ሲስተም ለማስገባት ከገንዘብ ሚኒስቴር በመጡ ባለሙያዎች ኦሬንቴሽን ተሰጠ፡፡

በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ገ/ምክኤል ወ/ገብርኤል እንዳሉት የተቀናጀ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ስርአት ለማስጀመር ወደ ዓዲግራት መምጣታች እናመሰግናለን ካሉ በኋላ የወረቀት ስራን በማስቀረት ወደ ሲስተም ማስገባት ፣ስራን አቀላጥፎ ለመስራት ጠቃሚ ቴክኖሎጂ መሆኑን ተናግረዋል።

ከገንዘብ ሚኒስቴር የተቀናጀ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ስርአት (FMISL) አይ ቤክስ ፅ/ቤት የIFMIS ትግበራን እውን ለማድረግ በዩኒቨርሲቲው የተሰሩ ስራዎችን አስመልክቶ ገለጻ ያደረጉት ኣቶ ሙኡዝ ገ/ሰላሴ የኢፍሚስ ፕሮጀክት ሮል አውት ቡድን መሪ እንደገለፁት በዩኒቨርሲቲው 6 ወር ቆይታ በማድረግ ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች ስልጠና የሚሰጡ መሆኑንና ሲስተሙን ከወረቀት ነፃ በሆነ መልኩ በዩኒቨርሲቲው መተግበር እንዲቻል የሚመለከታቸው አካላት እና የዩኒቨርሲቲ አመራሮች እንዲያውቁት የተደረገ ገለፃ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዕለቱም የኣካዳሚክና ምርምር ም/ኘሬዝደንት ዶ/ር ገ/ኪዳን ተስፋይ ጨምሮ የአስተዳደር ዘረፍ ሰራተኞች ፣ቡድን መሪዎች ፣ስራ አስፈፃሚዎች ፤ዳይሬክተሮች እና ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡በመጨረሻም የተለያዩ ጥያቄዎች ተጠይቀው መልስ ተሰጥቶባቸዋል ፡፡