ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ከፌደራል ግዥ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በኤለትሮኒክ ግዥ ዙርያ ለዩኒቨርስቲው ኣመራሮችና ኣቅራቢዎች ስልጠና መሰጠት ጀምሯል ።

በሃገር ደረጃ በተለይ ደሞ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲጅታላይዜሽን ስራ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል። ሁሉም ዓይነት የጨረታ ሂደቶች በኤለትሮኒክ ዘዴ እንዲገበያዩ የፌደራል ግዥ ባለስልጣን መመርያ በማዘጋጀት በውሱን ዩኒቨርሲቲዎች ስራ ጀምሯል። ዓዲግራት ዩኒቨርስቲም በሃገር ደረጃ ኤሌትሮኒክ ግዢ በውጤታማ መልኩ የጀመሩ ጥቂት ተቋማት ኣንዱ ነው።