የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስፖርት ልኡካን ቡድን

የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት ለስፖርት ልኡካን ቡድን የምስጋና መድረክ ኣዘጋጅቷል። በመድረኩ የተገኙት የዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት ዶ/ር ዛይድ ነጋሽ ለልኡኳን ቡድኑ ላስመዘገቡት ውጤት በውድድሩ ስለነበራቸው መልካም ስነምግባር ከፍተኛ ምስጋናቸውን ኣቅርቦላቸዋል።

በውድድር ወቅት ለተሳተፉ የሰርቲፊኬት ሽልማት የተሰጠ ሲሆን ወርቅና ነሓስ ላመጡ ተወዳዳሪዎች የተማሪዎች ህብረት የገንዘብ ሽልማት ኣበርክቶላችዋል።

በመጨረሻ የስፖርት ልኡካን የተሸለሙት ዋንጫ ለዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት ዶ/ር ዛይድ ነጋሽ ኣስረክበዋል።