በዶ/ር ጻሃዬ ተፈራ የተመሰረተውና የሚመራው ኢሲዲሲ (ECDC)የተሰኘው አገር በቀል ድርጅት በዓዲግራት ዩኒቨርስቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ስር ለሚገኘው የሳይንስ ሼርድ ካምፓስ ለማስተማርያነት አገልግሎቴ የሚውሉ ከ 6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ 30 ላፕቶፖችን ለዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ አበረከተ። ይህ ድጋፍ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ስር የሚገኘውን የስቴም ማእከል ለማጠናከር እና ለተማሪዎች የሚሰጠውን ትምህርት ጥራቱ ለማሳደግ ያለመ ነው። በስቴም ማዕከሉ የሚኖረው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ከመሆኑ በተጨማሪ፣ የሳይንስ ሼርድ ተማሪዎች በተግባር የተደገፈ ትምህርትን በጥራት እንዲያገኙ እና ዩኒቨርሲቲውም በሳይንስና ቴክኖሎጂ መስክ የተዘረጋ ትምህርት ለመስጠት እንዲችል ትልቅ ድጋፍ እንደሚሆን በዩኒቨርስቲው የስቴም ማእከል ኣስተባባሪ ኣቶ ሃፍቱ ተክላይ ገልፀውልናል።