07 Jul2018
የዓግራት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም አስመረቀ
የዓግራት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም አስመረቀ ዩኒቨርሲቲው ለ5ኛ ጊዜ በመደበኛና በተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ4,000 በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡ ከነዚህም መካከል 1,534 ሴቶች መሆናቸው ታውቋል፡፡ በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 43 የህግ ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን እነዚህ የህግ ትምህርት ተመራቂዎችም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የመውጫ ምዘና ወስደው 95 ፐርሰንት ያህሉ ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ2010 ዓ.ም ትምህርታቸውን አጠናቀው ለሚመረቁ ተማሪዎችና የተመራቂ ተማሪ ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ ይላል፡፡
Tags: https://www.facebook.com/pg/Adigrat-University-159643004188804