የዓዲ-ግራት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የብሔር ብሔረሰብ ብዓል ኣከበሩ።
በሃገር ደረጃ “በሕገመንግስታችን በደመቀ ሕብረ ብሄራውነታችን ለህዳስያችን” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ያለው የኢ/ያ ሕዝቦች ብሔር ብሔረሰብ ቀን በዓዲ-ግራት ዩኒቨርስቲም በተለያዩ ፕሮግራሞች ደምቆ ውሏል። “Multicultural Federalism In Ethiopia: A Response For Historic Discontent” የሚል መነሻ ፅሑፍም ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎበታል። በብዓሉ የተገኙ የዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት ክቡር ዶ/ር ዛይድ ነጋሽም ተማሪዎችን ሕገ መንግስት ያረጋገጠላቸው የእኩልነትና ዲሞክራሲያዊ መብት ጠብቀው በእርሰበርሳቸው ያለው ሰላም በማጠናከር ሃገሪቱን ለያዘችው የፈጣን ልማት ጉዞ የየራሳቸው ሚና ለመወጣት ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው መልእክታቸው ኣስተላልፏል። ተማሪዎቹን በበኩላቸው የብሔር ብሔረሰቦቸ ብዓል ስናከብር በመሃከላችን ያለው የእኩልነትና ዲሞክራሲያዊ መብት ይበልጥ ለማጠናከር የላቀ ድርሻ እንዳለው ተናግርዋል።