ዓዲ-ግራት ዩኒቨርሲቲ 3ኛውን የትግርኛ ቋንቋ ዕድገት ሲምፖዝዮም አካሄደ ።
ሲምፖዝዮሙ በየዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን ዘንድሮም ከመላው የክልሉ ከፍተኛ ትም/ት ተቋማት፣ኮሌጆች እና 2ኛ ደረጃ ትም/ት ቤቶች የተወጣጡ መምህራን፣ፀሃፊዎች፣ደረሲዎች እና ባለሙያዎች በመሳተፍ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ተካሂዷል ።
በሲምፖዝዮሙ ተገኘተው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያሰሙት የዩኒቨርሲቲው የኣካዳሚክ ም/ፕረዚዳንት ዶ/ር ኣለም መብራህቱ ሁሉም ተሳታፊና ባለ ድርሻ ኣካላት ትግርኛ በተፈለገው መንገድ እንዲያድግ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ጠይቀዋል። በተመሳሳይ መንገድ የዩኒቨርሲቲው ፕረዚዳንት ዶ/ር ዛይድ ነጋሽ ታዳሚዎችን በማመስገን ከፍተኛ የትም/ት ተቋማት እንደዚህ ዓይነት ሲምፖዝዮሞችና የምርምር ስራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ሃላፊነት የተሰጣቸው ከመሆኑ ኣንፃር ዩኒቨርሲቲያችንም እነሆ የትግራኛ ሲምፖዝዮም በማከናወን ዘንድሮ 3ኛ ዓመቱን አስቆጥሯል ። ስለሆነም ሁሉም መምህራኖች፣አመራሮች እና የባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና መጫወት እንዳለባቸው አሳስበዋል ።
በሲምፖዝዮሙ ላይ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች የቀረቡ ሲሆን በሶስቱም ዓመታት የጥናት ፅሁፍ ላቀረቡ ሙሁራን የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል ። ተሳታፊዎችም ዩኒቨርሲቲው ለትግርኛ ቋንቋ ዕድገት እየሰራው ያለውን ስራ በማድነቅ ስራው ቀጣይነት እንዲኖረው በመድረኩ ሃሳባቸው ገልፅዋል።