16 Mar2017
ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ኣለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 በደማቅ ሁኔታ ኣከበረ።
በዓሉ “የሴቶች የቁጠባ በህል ማሳደግ ለህዳስያችን መሰረት ነው” በሚል መሪ-ቃል ተከብሯል። ዩኒቨርስቲው በየዓመቱ የሴቶች ቀን ሲያከብር ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ሴት ተማሪዎችና ድገፍ ላደረጉ ሴት መምህራን ማበረታቻ ሽልማት የሚሰጥ ሲሆን ዘንድሮም በተመሳሳይ ሁኔታ ከየኮሌጁ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እና ድጋፍ ላደረጉ መምህራን የቦንድ ሽልማት ከዩኒቨርስቲው ፕረዚደንት ደ/ር ዛይድ ነጋሽ ተበርክቶላቿል ። በዓሉ የዩኒቨርስቲው ማሕበረሰብ በተገኘበት በተለያዩ ፕሮግራሞች በደማቅ ሁኔታ ተከበሯል ።