ኣስደሳች ዜና ለሁለም የዩኒቨርስቲው ማሕበረሰብ
ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ በትምርት ልማት ሰራዊት ግንባታ (Cooperative Learning) እየሰራው ያለው ኣስደናቂ ስራ በደሴ ከተማ በወሎ ዩኒቨርስቲ ኣዘጋጅነት እየተካሄደ ያለው የኣጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ ጉባኤ በኣርኣያነ ቀርበዋል ። ክቡር ደ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም የትምህርት ሚኒስተር ምኒስትር እንዳሉት ዓዲ-ግራት ዩኒቨርስቲ እየሰራው ያለው ኣስደናቂ ስራ ከላይ እስከ ታች ያው ኣመራሩና ማሕበረሰቡ በቁርጠኝነት ስለ ስራ ነውና ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ስራው በቁርጠኝነት እንዲሰሩት ኣሳስብዋል። የጉባዔው ተሳታፊዎች ዩኒቨርስቲው እየሰራው ያለው ስራ ለሁሉም የትምህርት ተቋማት ተመኩሮውን ማስፋፋት እንዳለበት ኣንስተው ማብራርያ የሚያስፈልጋቸው የተለያዩ ጥያቄዎች እንስትዋል ። ለተነሱ ጥያቄዎች የዩኒቨርስቲያችን ፕረዚዳንት ደ/ር ዛይድ ነጋሽ ማብራርያ ሰጥቷል። በጉባዔው ተሳታፊ የነበሩ ኣካላት የሚከተሉት ናቸው ።
- የዩኒቨርስቲዎች ከፍተኛ ኣመራሮች
- የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ኣባላት ተወካዮች
- የ ኣጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ ሓላፊዎች
- የቴክኒክና ሙያና ስልጠና ሓላፊዎች
- የኢህኣዴግ ፅ/ቤት ተወካዮች
- የህዝብ ክንፎች
- የፌዴራል ሚኒስተር መስራቤቶች ባለሙያዎች
- የመምህራን ማሕበር ሓላፊዎች
- የኢትዮጵያ ተማሪዎች ሕብረት
- የተለያዩ የሚድያ ተቋማት ተወካዮች
ዓዲ-ግራት ዩኒቨርስቲ የህዝብና ዓለም ኣቀፍ ግንኙነት ፅ/ቤት ከወሎ ዩኒቨርስቲ