20 Mar2017
በዓዲግራት ዩኒቨርስቲ የጥልቅ ተሃድሶ መድረክ ተጠናቀቀ።
በዓዲ-ግራት ዩኒቨርስቲ ሲካሄድ የሰነበተው የኣስተማሪዎች፤ የሰራተኞችና የተማሪዎች የጥልቅ ተሃድሶ መድረክ በውጤታማ መልኩ ተጠናቀቀ። የዩኒቨርስቲው ማሕበረሰብ ኣባላት በተለየ መልኩ ከኣመለካከት፤ ተልዕኮን በተሳካ መልኩ መፈፀም፤ ኪራይ ሰብሳቢነት ከመታገልና ከስነምግባር ጋር በተያያዙ ጉዳዮች እርሰበርሳቸው የተገማገሙበትና ሁሉም ማሕበረሰብ ራሱን የፈተሸበት ውጤታማ መድረክ ሁኖ ኣልፏል። በመድረኩ ከ 10,000 በላይ ተማሪዎችና ከ 2000 በላይ የሚሆኑ ሰራተኞቸ ተሳታፊዎች ነበሩ።