በዓዲግራት ዩኒቨርስቲ የሰላም ቀን ተከበረ
በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በቀን 27/08/10 ዓ/ም “ገንዘባችንና ዕውቀታችን ወደ ፍሬ የሚቀየረው ሰላም ሲኖር ብቻ ነው” በሚል መሪ ቃል በድምቀት የተከበረው የሰላም ቀን ከጥዋቱ 2፡30 ጀምሮ በዓዲግራት ዩኒቭርስቲው ወስጥ በመመረቂያ አዳራሸ በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡ በብዓሉ ላይ በርካታ ተማሪዎችና ከዓዲግራት ከተማ ከተለያዩ ተቋማት የተጋበዙ እንግዶች፤ ተሳትፈውበታል፡፡ ከተሳታፊዎች መካከልም የሀገር ሽማግሌዎች፤ የሃይማኖት አባቶች፤ ፣የ11ኛ ክፍለ ጦር የሀገር መከላከያ ሰራዋቶች፡፡ የምስራቃዊ ዞን ዓዲግራት ከተማ ከፍተኛ አመራሮ ፡ ትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንደሁም ከምስራቃዊ ዞን የግጭት መከላከልና አፈታት ጉዳይ ቢሮ የመጡ ተወካዮች፤ ከመቀለና ከአክሱም ዩኒቨርስቲ የመጡ የሰላም ፎርም ሰብሳቢዎች፤ እንዲሁም የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል፡፡ በዓሉን ያዘጋጀው የሰላም ፎርም ፅ/ቤትን ጨምሮ ሌሎችም በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያሉ አደረጃጀት እና ክበባትም የበዓሉ አዳማቂዎች ሆነው ውለዋል፡፡ በዚህ በዓል ላይ የተለያዩ ፕሮግራሞች የቀረቡ ሲሆን ከነዚህም መካከል በዋናነት ከትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የመጡት በአቶ አሰፋዉ ምለሹ የመክፈቻ ንግግር የተጀመረ ሲሆን የፓናል ዉይይት ፡ ስነ ፅኁፍ ፡ ድራማና ሙዚቃዎች ለበዓሉ ከፍተኛ ድምቀት ሰጥተዉታል፡፡ በተጨማሪም ስለ ሃገራዊ ሰላም የሚሰብኩ በርካታ ቁም ነገሮችን የያዘውና በሰላም ፎረም ፅ/ቤት የተዘጋጀ ብሮሸር (በራሪ ወረቀት) ለታዳሚው ተሰራጭቷል፡፡ በተለይም ደግሞ በስነ-ዜጋና ሰነ-ምግባር ትምህርት ክፍል ሃላፊ በሆኑት በአቶ ግርማይ ታደለ የቀረበዉ እና በሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ በሚያጠነጥነው የፓናል ዉይይት ላይ ብዙ አንኳር ነጥቦች፤ ቁምነገሮች እና መልዕክቶች ተላልፈዉበታል፡፡ በተለይ የሰላም እሴት ግንባታን በማጠናከር ልማትን እንዴት ማስቀጠል እንዳለብንና ሁሉም የባለድርሻ አካላት የበኩሉን ድርሻ በመወጣት በድርድርና በዉይይት የሚያምን ሀገር ተረካቢ የሰላም አምባሳደር ዜጎችን በመፍጠር የሀገራችን እድገት እናስቀጥል የሚል ይዘት ሲኖረዉ ከባለድርሻ አካላትም የተለያዩ ሓሳብና አስተያየቶች ቀርቧል ፡፡
ለምሳሌ
ከሃገር ሽማግሌዎች – ልጆቻችን በመምከርና በማስተማር በጥሩ ስብዕና ልናሳድግ ይገባል ፡፡
ከ11ኛዉ ክፍለ ጦር የሃገር መከላከያ ሰራዊት – በየትኛዉም ጊዜና ሁኔታ መሪ ወይንም የሃገር ገዥ ሊቀያየር ይችላል፡፡ ቢሆንም ግን ሁሌም ለሰላም ዘብ በመቆም የሀገራችን ህዳሴ ወደ ፊት እንዲቀጥል ማድረግ እንጂ መሪ በተቀየረ ቁጥር ወደ ኃላ እያሰብን የጀመርነዉን የእድገት ጎዳና እሾህ ልንተክልበት አይገባም እኛም ሁሌ ከህዝባችን ጎን ሆነን ሰላማችን እንጠብቃለን ብለዋል፡፡
ከኃይማኖት አባቶች – ኢትዮያ የሃይማኖት፤ የብሔር፤ የቋንቋ ልዩነት ያሏት ሃገር ብትሆንም በኃማኖታችን መፀለይ በልዩነታችን መኩራት እንጂ አንዱ ሌላዉን በማጥላላት ሰላማችን ማጣት የለብንም የሚል መልክት አስተላልፈዋል፡፡ ከሌሎች አካለትም ለሰላም ሁሉም የራሱን ኃላፊነት በመዉሰድ በፍቅር በመተባበር ፤በመቻቻልና በመዋደድ የተመሰረተች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትዉልድ ልናወርስ ይገባል ብለዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር በድራማዉ በስነ-ጽሁፉና በሙዚቃዊ ስልቱ በርካታ ስላለም ስለ ሰላም የሚያበስሩ መልዕክቶች ከመተላለፋችውም በተጨማሪ የፕሮግራሙ አዘጋጅ የሆነው የሰላም ፎርም ጽ/ቤት በሚሰራቸው የሰላም እሴት ግንባታ ላይ ትልቅ አስተዋፅዖ ላደረጉ ባለድረሻ አካላት ያዘጋጀዉን የምስጋና ምስክር ወረቀት አበርክቷል፡፡ እነዚህንና ሌሎች በርካታ መልክቶች ከተላለፉ በኋላ በሰላም ፎርም ጽ/ቤት ፕረዚዳንት በተማሪ ዋሴ ሲሳይ የመዝጊያ ንግግር ከተደረገ በኋላ ለእንግዶች የምሳ ግብዣ ተደርጎ ፕሮግራሙ ከቀኑ 7፡30 ላይ ተጠናቋል፡፡