በለውጥ መሳርያዎች ኣተገባበር ዙርያ ስልጠና ተሰጠ
የዩኒቨርስቲው የእቅድና ተቃማዊ ለውጥ ከሰውሃይል ፅ/ት በጋራ በመሆን ለዩኒቨርስቲው ከፍተኛ ኣመራሮች፣ ዲኖችና ዳይረክተሮች፣ ፅ/ት ሓላፊዎች እንዲሁም የትምህርት ክፍል ሓላፊዎች የሶስት ቀናት ስልጠና ሰጥቷል።የስልጠና ርዕሶች የለውጥ መሳርያዎች ምንነት ኣስፈላጊነትና ትስስር፣የዜጎች ቻርተር፣ የመልካም ኣስተዳድር ጉዳዮች፣ የስነ ምግባር ኮድና ኣዲሱ የመንግስት ሰራተኞች ኣዋጅ 1064/2010፣ የስብሰባ ኣስፈላጊነትና ኣተገባበርና የውጤት ተኮር ስርዓት ናቸው።
ስልጠናው የሰጡት በፌደራል መንግስት ሰልጥነው የመጡ የዩኒቨርስቲው ሰራተኞች ሲሆኑ ከእቅድና ተቋማዊ ለውጥና የሰው ሃይል ፅ/ቤቶች መሆናቸው የስልጠናው ኣስተባባሪ የዩኒቨርስቲው የእቅድና ተቋማዊ ለውጥ ፅ/ት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ተክሉ ገልፀውሉናል። ሰልጣኞቸ ሰልጥነው ከስራቸው ያሉ ሰራተኞች እንዲያሰለጥኑና ሁሉም የዩኒቨርስቲው ማሕበረሰብ ወደ ተግባር ለውጦ የተሻለ ዩኒቨርስቲ ለማድረግ ኣላማ ይዞ መሆኑ ሓላፊዋ ገልፃልናለች።