ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ የኢትዮ-ኤርትራ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ ኣካሂድዋል
ዩኒቨርስቲው “የኢትዮ-ኤርትራ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለዘላቂ ሰላም” በሚል መሪ ቃል ኣውደ ጥናት ኣካሂዷል። በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርስቲው ግዝያዊ ፕረዚዳንት ዶ/ር ገ/መስቀል ገ/ፃድቅ የሰላም ጉዳይ የውስን ሰው ጉዳይ ሳይሆን የሁሉም ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት የተናገሩ ሲሆን ኣክለውም ቡለቱም ህዝቦች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለሚያካሂዱት ተመራማሪዎች ዩኒቨርስቲው ኣስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፅዋል።
በመድረኩ የክብር እንግዳ የነበሩ የህወሓት ስራ ኣስፈፃሚ ኮሚቴ ኣባል ኣቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው የኢትዮ-ኤርትራ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በዘላቂነት እንዲጠናከር የሁለቱም ሃገራት ህዝቦች በላቀ ትኩረት መስራት እንዳለባቸው ተናግረው የሁለቱም ህዝብ በጋራ ጥቅሞችና በታሪክ የተሳሰሩ በመሆናቸው ለሰላምና ለህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው ገልፅዋል።
በመድረኩ ከ80 በላይ ኤርትራውያን፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲ የመጡ እንግዶች፣ ኣስተማሪዎችና ተማሪዎች ተሳታፊዎች ነበሩ።